ቱ. ማ. ኢ ጥቅምት 29/2015 ዓ ም የምክክር መድረኩን የከፈቱት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ነጋሽ እንደገለጹት ከሆቴሎችና ከቱሪዝም አስጎብኝ ድርጅቶች ጋር ቅንጅታዊ አሰራር በመፍጠር የሚሰሩ ስራዎች ሁሉ ጠቀሜታው ለሁሉም መሆኑን በመግለፅ የዛሬውን ውይይት በሙሉ ልብ እንዲሳተፉ አሳስበዋል።

ለውይይት የቀረቡ ሰነዶች የኢንስቲትዩቱ አደረጃጀት በምርምርና ማማከር አገልግሎት በቅንጅት የሚከናወንበትን ሂደት ፣ የተከለሰውን የሙያ ደረጃና ሥርዓተ ስልጠና እንዲሁም የትብብር ስልጠና ማስተግበሪያ አስፈላጊነት በሚሉ ርዕሶች የተዘጋጁ ሰነዶች በተከታታይ ቀርበው ገለጻ ተደርጎባቸዋል።
በሰነዶቹ የትብብር ሰልጠናው ለአንድ ወገን ብቻ የሚጠቅም ሳይሆን ለሆቴልና ቱሪዝም ድርጅቶች ፣ ለቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩትና ለሰልጣኞችም የሚጠቅም መሆኑን በመግለጽ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ እጅጉን ወሳኝ መሆኑም ተጠቅሷል።
በቀረቡ ሰነዶች ጥያቄና አስተያየት የሰጡ አብዛኞቹ የሆቴል ሥራ አስኪያጆችና የቱሪዝም አስጎብኝ ድርጅቶች የተቋሙ የቀድሞ ሰልጣኞች መሆናቸውን በመግለጽ አሁን የተከለሰውን የሥልጠና ሥርዓተ ትምህርት መዘጋጀቱን አድንቀው ክፍተት የሚታይባቸው የሙያ ዘርፎችም በስርዓተ ስልጠናው እንዲካተቱ ሀሳብ ሰጥተዋል።
በመጨረሻም ኢንስቲትዩቱ ከባለድርሻ አካላቱ ጋር የግንኙነት ጊዜ እንደሚያመቻችና ሁሉም ተሳታፊ በመሆን የዘርፉን የሰለጠነ የሰው ኃይል እጥረት ለመሙላት ከመንግስት ጎን በመቆም የበኩላቸውን እንዲያበረክቱ ጥሪ ተላልፎላቸዋል።