ቱ. ማ. ኢ ጥቅምት 23/2015 ዓ.ም ቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ጋር በመተባበር ሥራ አጥ የሆኑ ከአስረኛ ክፍል በላይ የትምህርት ዝግጅት ያላቸውና ከአረብ አገር ተመላሾች ያሉበት15 ሰልጣኞች ለ10 ተከታታይ ቀናት ሰልጠና ወስደው ተመርቀዋል፡፡

ስልጠናው ፈጣን ምግቦችን አዘጋጀቶ በጎዳና ላይ በመሸጥ ገቢ ሊያስገኝ የሚያስችል ሲሆን፤ ይህን ስልጠና የሰጡት አሰልጣኝ ወ/ሮ ንግስቲ ግደይ አንጋፋ ባለሙያ እና በማሰልጠኛ ተቋሙ የረጅም ዘመን አገልግሎት ያላቸው በመሆኑ ስልጠና ለወስዱትም ሰልጣኞች ከጎዳና ምግብ ዝግጅት ባሻገር የተሻለ ሥራ በመስራት የተሻለ ገቢ የሚያገኙበት እንደሆነ ሰልጣኞች ገልጸዋል፡፡
ኢንስቲትዩቱ በወረዳው የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን ወደፊትም ለህብረተሰቡ ተደራሽ የሚሆኑ አገልግሎቶችን ለመስራት ዝግጁ መሆኑን የተቋሙ የስልጠናና አቅም ግንባታ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት ተናግረዋል፡፡