የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩትና ገነት ሆቴል በጋራ ሆነው በጦርነቱ ለተጎዱ ወገኖችና ለመከላከያ ሰራዊት ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ግምት ያለው የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ፡፡

በርክብክቡ የተገኙት በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ተሻለ በሬቻ እንደገለጹት ይህ ድጋፍ የመጀመሪያም የመጨረሻም ሳይሆን ዘላቂነት ያለው እንደሚሆንና ለተጎዱ ወገኖችና ለመከላከያ ሰራዊት ሁል ጊዜም ድጋፋችን እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
በተቋማችን የተዘጋጁ ኩኪስ፣ ቴምር፣ ፓስታ እና የፉርኖ ዱቄት ሲሆን በገንዘብ ሲሰላ ከ1.5 ሚሊየን የሚገመት ቁሳስ ድጋፍ ተደርጓል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከ33 ሚሊየን በገንዘብ ካደረጉት ድጋፍ በተጨማሪ ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን 4.83 ሚሊየን የሚጠጋ የምግብ አይነቶች ድጋፍ እንደተደረገ ተገልጿል፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የመከላከያ ሚኒስተር ዴኤታ ወ/ሮ ማርታ ሉጂ ናቸው፡፡