የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት ሰልጣኞችና ሰራተኞች 43ኛውን ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን (March 8) “የላቀ ትኩረትና ቁርጠኝነት ለሴቶች ሁለንትናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት” በሚል መሪ ቃል በገነት ሆቴል አከበሩ፡፡
በዓሉ በአገራችን ለ43ኛ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ108ኛ ጊዜ የሚከበር ሲሆን በዋነኝነት በሴቶች ላይ ይደርስ የነበረውን ጭቆና ለማስወገድ የተደረገውን ሁለንትናዊ እንቅስቃሴና ውጤት ከመዘከር ባለፈ ሴቶች ከነበረባቸው ጭቆና ተላቀው በኢኮኖሚያዊ፣ በማህበራዊነና በፖለቲካዊ መስኮች እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ የሚሆኑበትና የጾታ እኩልነት የሰፈነበት ምቹ ሁኔታን የመፍጠር አላማን ሰንቆ የሚከበር ተላቅ ሁነት ነው፡፡
በዓሉን በንግግር የከፈቱት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አስቴር ዳዊት የኢንስቲትዩቱ ሴት ሰልጣኞች ለሁለንትናዊ እኩል ተጠቃሚነት እራሳቸውን ማብቃት አለባቸው፣ ለተለያዩ በሽታዎች ከሚዳርጉ ሁኔታዎችም መራቅ አለባቸው ብለዋል፡፡
በበዓል አከባበሩ ላይ በአንጋፋና ተወዳጅ አርትስቶችና ታዋቂ ግለሰቦች በበጎ ፍቃድ የደም ልገሳና የኤች.አይ.ቪ ኤድስ ቫይረስ ላይ ያተኮረ የልምድና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎች ተሰጥተዋል፡፡
ከዚህም ባሸገር አንጋፋና ተወዳጅ አርትስቶችና ታዋቂ ግለሰቦች ለሰልጣኞች ምክር ለገግሰዋል፡፡