ሆ.ቱ.ሥ.ማ.ኢ ግንቦት 01/2011 ዓ.ም የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 50ኛ ዓመት የወርቅ እዮበልዮ በዓል ዝግጅትን በደማቅ ሁኔታ ለማክበር የግንዛቤ ማስጨበጫና የማነቃቀያ መርሐግብር ተጀምሯል፡፡
የ50ኛ ዓመት የወርቅ እዮበልዮ በዓል ዝግጅት ዋና ዓላማ የማሰልጠኛ ኢንስቲትዩቱን ሀምሳ ዓመት ጉዞን አስመልክቶ በስልጠና ዘርፉ ያጋጠሙ ችግሮችን በመለየት የቀጣይ ስራ አቅጣጫ ግብዓት ለማሰባሰብ መሆኑን የኢንስቲትቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አስቴር ዳዊት ገልጸዋል፡፡
በመሆኑም በዚህ የተቋሙ 50ኛ ዓመት የወርቅ እዮበልዮ በዓል ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በመሳተፍ ለኢንስቲትዩቱ ቀጣይ እድገት አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥሪያቸውን አስተላልፏል፡፡

በዓሉ ከሰኔ 01-03 /2011 ዓ.ም የሚከበር ሲሆን በዘርፉ ምሁራን የተዘጋጀ የጥናትና ምርምር ስራዎች የሚቀርቡበት ታላቅ ጉባኤ የተዘጋጀበት፣ ቀጣሪ ድርጅቶችና ስራ ፈላጊዎች የሚገናኙበት (job fair), ኤግዝቢሽን፣ የተለያዩ መዝናኛዎች እና ሌሎችም ዝግጅቶች የሚቀርቡበት በዓል ነው፡፡